Please take the time and kindly share your thoughts and feelings.

Friends & Family Comments

  1. ሰይፉ ጢቦ መሞቱን ሰማሁ፣ ነፍሱን ይማረው ፣ለቤተሰቦቹም ጥናቱን ይስጥ ሌላ ምን ይባላል

  2. እንደመሰለኝ ፣ #ሰይፉጢቦ የሚኒልክ ሆስፒታል ሰፈር ልጅ ነበር ጃንሜዳ ዙርያ ። ለቀኃሥ ኮከበ ጽባህ ትምህርት ቤት ቅርብ ሆኖ ሳለ ፣ እሱ ግን ይማር የነበረው ዳግማዊ ሚኒልክ ትምህርት ቤት ነበር ።

    በዚያን ወቅት ፣ የሚኒልክ ትምህርት ቤት ጉልቤው ሰይፉ ጢቦ ሲሆን ፣ የቀኃሥ ጉልቤ የነበረው ደግሞ #ሰገደ ነበር ።
    አይ ልጅነት ! ሰገደና ፥ ሰይፉ ጢቦ ! የመፋለሚያ ቦሩ ሜዳ ሲፈልጉ ማዋገሪያው ሜዳ የቀኃሥ ትምህርት ቤት ኳስ ሜዳ ነበር ።

    የሚኒሊክ ተማሪዎች ሰይፉ ጢቦን አጅበው ወደ ቀበና ይመጣሉ ። የቀበና ዙርያ ልጆችና የኮከበ ጽባህ ተማሪዎች ደግሞ ሰገደን አጅበን ይዋጣላችሁ እያልን ! በአፋጨው አጋጨው ስታይል ዙሩን እናከረዋለን ።

    እንደኩይሳ ክምር ግዙፉና ቦዲ የነበረው ባለ ግርማ ሞገሱ ሰይፉ ጢቦና ፥ ጭባ መሳይ ቀጭኑ የጅዶው ሊቅ ሰገደ ወደ ፍልሚያው የቀኃሥ ትምህርት ቤት ቦሩ ሜዳ ሲገቡ ! ፉጨቱና ጩኽቱ ይበረክታል ። ሚኒልኮች ለጢቦ – ቀኃሦች ደግሞ ለሰገደ ። አንዳንዴ አላደርስ ብሏቸው ከዶሮ ተራው ጀምሮ ርኩቻውን ሊጀምሩ ሲሉ በገላጋይ ይለያያሉ ። ያ ! ጊዜ ትዝ ይለኛል ።

    (english translation)
    In my opinion, Seifu Tibbo was a boy that grew up around Menelik Hospital close to ‘JanMedda’. Even though he lived closer to “Kehas Kokobe Tsibah’ school, he used to go to Menilik school. At that time the bossy person in Menelik school was seifu Tibbo. On the other hand in “Kehas Kokobe TSebeha’ school Segede was the tough guy.
    Crazy youth era! Segede and Seifu Tibbo!! When they searched on where to do the duel, it was decided it is going to be in the ‘Kehas’ soccer field.

    Then Menelik’s students accompanied their hero Seifu and came to ‘Kebena’. Kids from Kebena and ‘Kehas’ students flocked around Segede shouting ‘Let us do it! Let’s get them!’ with whistle and all!
    The graceful and imposing Seifu was going to meet the skinny and judo professional. Seifu and Segede entered the Boru field for the duel. The yelling and whistling were out of control from supporters so much that some of them would start their own skirmish not being able to wait for the fight to start… but people would separate them.
    That, I vividly remember.
    We just heard Seifu Tibbo passed away two days ago, we don’t have any information about the service. May he rest in peace! Condolences to his family.

  3. እኔ ግን ሰይፈን በሩቅ የማዉቀዉ አዲስ ከተማ ድሮ ከፍተኛ 4 ቀበሌ 26 በሚባለዉ አካባቢ አዴ ሜዳ ተብሎ ወይም መልሴ ዳቦ ቤት አካባቢ ይመስለኝ ነበር፡፡ ሌላ ሰይፈ የሚባል ቦክሰኛ ከሆነ አላዉቅም፣ ሞስኮ ኦሎምፒክ ሁሉ እንደተሳተፈ ነዉ የማስታዉሰዉ፡፡ለማንኛዉም ነፍስ ይማር፡፡

  4. ለአዲስ አበባ ልጅ በጊዜው የሰይፉ ጢቦን ስም መስማት አዲስ ነገር አልነበረም በጣም ታዋቂ ሰው ነበር!ነፍስ ይማር ! ለቤተሰቦችም መፅናናትን ይስጥልን!

  5. ልጆች ሖነን የምናሥታውሰው ጢቦ አና ሰገደ የቅምብቢት ሠፈር ልጅ አሥታውሰዋለሁ ወወክማ ያፈራቸው በዛ ግዜ የነበሩ ታላላቅ ወንድሞቻችን ሳስብ ለወገን የሚቆረቆሩ በአካል በመንፈሥ ብቁ የነበሩ ነበር ፈጣሪ ነፍሡን ይማረው።

  6. ነፍሱን ይማር ከኔ 3 አመት በኋላ የምኒልክን ተማሪ ነበር

Join the Conversation, Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *