የሕይወት ታሪክ

አቶ ሰይፉ መኮንን ከአባታቸው ከአቶ መኮንን ተፈራ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ቀነኔ በላቸው ሰኔ 3፣ 1945 ዓ.ም. በሸዋ አውራጃ በአላልቶ ከተማ ተወለዱ። እድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ በየነ መርድ ትምህርት ቤት ያጠናቀቁ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ አዲስ አበባ በሚገኘው በዳግማዊ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቀዋል።
አቶ ሰየፉ መኮንን ገና በልጅነታቸው ተፈጥሮ ባደላቸው ለእስፖርት የሚስማማ ቁመና የተነሳ እስፖርት በተለይ ሰውነት መገንባት፡ እግር ኳስ እና ቦክስ መወዳደር በጣም ይወዱ ነበር።
አቶ ሰይፉ ገና የአስራ ሶስት አመት ወጣት በነበሩበት ወቅት አራት ኪሎ ባለው ወወክማ ገብተው ብረት በማንሳትና የተለያዩ ጅምናስቲክ በማድረግ ሰውነታቸውን መገንባት ተያያዙ። በጊዜው የአማርኛ አስተማሪያቸው የነበሩት የሰውነታቸውን እርዝማኔና እና የጡንቻቸውን መፈርጠም አይተው ጢቦ ብለው እስከ አሁን ድርስ የሚጠሩበትን የቅጽል ስም አወጡላቸው። ከእዛ ጅምሮ አቶ ሰይፉ መኮንን ከመባል በላይ ሰይፉ ጢቦ በመባል ይታወቃሉ። አቶ ሰይፉ በነበራቸው የክብደት ማንሳት ፍላጎት እና ፍቅር በአጭር ጊዜ አዲስ አበባ ውስጥ የታወቁ ቦዲ ቢልደር ሆኑ።
በአስራ ሰባት አመታቸው እዛው አራት ኪሎ ወወክማ ስፖርት ሲሰራ ሁልጊዜ ይመለከታቸው የነበረ አሜሪዊ የቦክስ አሰልጣኝ ኤድዋርድ ሳይመን ቦክስ እንዲጫወቱ ጋበዛቸው። አቶ ሰይፉም ጥቂት ቀን ካሰቡ በዋላ ግብዣውን ተቀብለው ልምምድ ማድረጉን ጀመሩ። ለጥቂት ጊዜ በኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን ውስጥ ጠንካራ ልምምድ እና ውድድር ካደረጉ በኋላ፤ አዲስ አበባ ከሚገኘው የጀርመን ስፖርት ሚንስትሪ፡ ጀርመን አገር በርሊን ከተማ ሄደው ከፍተኛ የቦክስ ትምህርት እና ውድድር እንዲያደርጉ ስኮላርሽፕ አገኙ።
ከጀርመን ተመልሰው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ በጎን ቦክሱን በከፍተኛ ደረጃ በመለማመደ ለ1964 ዓ.ም. ጀርመን ሚውኒክ ኦሎምፒክ ለመወዳደር ብቁ ሆኑ።ሚውኒክ ውድድር ላይ የመጀመሪያውን ሶስት ውድድር አሸንፈው አራተኛውን በትንሽ ነጥብ በመሸነፍ የአገራቸውን ሰም በመልካም አስጠርተዋል። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ሲመለሱ ከግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ መዳልያ ተሸልመዋል። በ1965 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በተደረገው የምስራቅ እና የመካከለኛው አፍሪካ የቦክስ ውድድር በራሳቸው የክብደት መደብ የኬንያን እና የኡጋንዳ ሐይለኛ ተወዳዳሪዎችን በማሸነፍ የወርቅ መዳልያ ተሸልመዋል።አቶ ሰይፉ በጥሩ ሁኔታ ላይ እያሉ የደርግ መንግስት 1966 ዓ.ም. መጣ። በደርግ መንግስት ዘመን ትንሽ እንደቆዩ አቶ ሰይፉ ከአክስታቸው ልጅ ጋር ሆነው ወደ ኬንያ

ተሰደዱ። ኬንያ ውስጥ በቆዩበት ጊዜ የሚወዱትን ቦክስ ልምምድ እና ውድድር ቀጥለውበት ኬንያን በመውከል ታንዚያ እና ዛምቢያ በመሄድ ተወዳድረው ጥሩ ውጤት አግኝተዋል። በዚህም ምክንያት ከኬንያ ፕሬዜዳንት ጆሞ ኬንያታ ሽልማት አግኝተዋል። በ1968 ዓ.ም. በኬንያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ፡ ኢትዮጵያን ወክለው ካናዳ ለሚደረገው ኦሎምፒክ እንዲወዳደሩ ግብዣ ቀረበላችው። አገራቸውን የሚወዱት ወጣት አለምንም ማቅማማት ኢትዮጵያ ተመልሰው ልምምዱን ቀጠሉ። በማካከሉ ደቡብ አፍሪካ ለካናዳ ኦሎምፒክ እንደምትወዳደር ሲረጋግጥ አብዛኛው የአፍሪካ አገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ አፓርታይድን በመቃወም አድማ በመምታት ላይወዳደሩ ወሰኑ። በዚህ የተነሳ የእርሳቸውም ህልም እውን ሳይሆን ቀረ። በሁለት ዓመት የኢትዮጵያ ቆይታቸው በሁላ የደርግ መንግስት የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝነት ስራ ሰጣቸው። በ1970 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ራሽያ ለከፍተኛ ቦክስ ስልጠና ላካቸው። ከራሽያ እንደተመለሱ ብዙም ሳይቆዩ ኢትዮጵያ በቀይ ሽብር መታመስ ጀመረች። አቶ ሰይፉም ኢሕአፓን ትደግፋለህ በመባል እስር ቤት ተጣሉ። ከሶስት ወር እስር በኋላ ሊቢያ ላይ ለሚደረገው የአፍሪካ ቦክስ ውድድር መዘጋጀቱን ተያያዙት። የደርግ መንግስት ከኪውባ መንግስት ጋር በነበረው ወዳጅነት መሰረት አቶ ሰይፉ እና ሌሎች ወጣቶች ወደ ኪውባ ለአንድ ወር የመጨረሻ ልምምድ አድርገው በዛው ሊቢያ እንዲሄዱተፈቀደላቸው። ከአንድ ወር የኪውባ ቆይታ በኋላ አቶ ሰይፉ እና ሁለት ጓደኛ ቦክስ ተጨዋቾች ወደ ሊቢያ ጉዞ ላይ አውራፕላኑ ለነዳጅ ሞንትርያል ካናዳ ሲያቆም ወርደው ሳይመለሱ ጥገኝነት በመጠየቅ ካናዳ ቀሩ። ከአንድ አመት ካናዳ ቆይታ በኋላ 1972 ዓ.ም. ሎሳንጀለስ የሚኖረውን የአክስታቸውን ልጅ ለመቀላቀል አሜሪካ ገቡ። አሜሪካ ውስጥ የግል ስራ በመስራት እራሳቸውን ሲደግፉ ቆይተዋል። አቶ ሰይፉ ሁልጊዜ በፍቅር የሚያስቡት በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በእርሳቸው አነሳሽነትና ንቁ ትሳትፎ በዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄደውን የ10000 ሜትር የሩጫ ውድድር ፕሮግራም ነው። ይህ በአበበ ቢቂላ ስም የተሰየመውና በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈ ፕሮግራም ለአቶ ሰይፉ የመንፈስ እርካታ ይሰጣቸው ነበር። አቶ ሰይፉ መኮንን የድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን የመጀመሪያው ቦርድ አባል በመሆን ለአምስት ዐመት አገልግለዋል። አቶ ሰይፉ መኮንን ትዳር ይዘው የአንድ ወንድ ልጅና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበሩ። አቶ ሰይፉ መኮንን ለረጅም ጊዜ ባደረባቸው የኩላሊት በሽታ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ማክሰኞ ሰኔ 9፡ 2012 በ67 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አቶ ሰይፉ እናት፡ ሁለት እህቶች፡ አንድ ወንድ የልጅ ልጅ አላቸው።

እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማርልን።

BIO

Seifu Mekonnen , the beloved son of Ato Mekonnen Tefera and W/O Kenene Belachew was born on June 11, 1953 in a city called Alalto in the former province of Sehwa, Ethiopia. He attended elementary school at Beyene Mered in Addis Abeba, Ethiopia and continued his high school studies at the well known Dagmawi Minilik Secondary School. Seifu’s interest in sports began at an early age where he participated in numerous sports particularly soccer and body building. At the early age of 17 Seifu joined the Arat Kilo YMCA where he continued to participate in the sports of body building and gymnastics. A teacher who noticed his physical build gave him the nickname “Tibo”, which stuck to this day and everyone affectionately calls him Seifu Tibo since that time. While at YMCA he was noticed by an American boxing coach named Edward Simon who invited Seifu to try competitive boxing. Needless to say he loved boxing and he exceled at it in no time. After practicing with the Ethiopian Boxing Federation for a short time, he was awarded a boxing scholarship in Berlin, Germany largely due to the German Embassy in Addis Abeba at the time.

After a brief stay in Germany, he returned to Ethiopia, continued his high school education while still training and participating in boxing matches. In 1972 he was chosen to attend the Olympic Games in Munich, Germany and represented his country with pride. At the Olympics he won his first three matches convincingly and lost his fourth one in a very close match.Upon his return from the Olympics, he was awarded a medal from His Imperial Majesty Haile Selassie I and in 1973 he won a gold medal at the Eastern and Central Africa Boxing Tournament held in Addis Abeba defeating talented boxers from Kenya and Uganda. In 1975 during the Derg era he was forced into exile to Kenya with some close relatives. He continued the sport of boxing while in Kenya. He even represented Kenya in boxing matches that were held in Kenya and Zambia. He was given a recognition award from
President Jomo Kenyatta.In 1976 the Ethiopian Embassy in Kenya extended an invitation to Seifu to participate at the Olympic that was to take place in Canada. Seifu accepted the invitation and started to prepare. Unfortunately, Ethiopia and several other countries boycotted the games due to the invitation of the then apartheid government of South Africa and Seifu was not able to attend.

After he returned to Ethiopia he began to work as a trainer with young boxers and in 1978 he was sent to Russia for more studies to help him become a better trainer. As soon as he returned from Russia the infamous Red Terror took place in Ethiopia and Seifu spent some time in prison accused of supporting EPRP. After his release from prison, he began training for a boxing tournament in Libya and as preparation for the tournament he along with two other boxers were sent to Cuba for extra training. On their way to Libya, while his plane stopped in Canada for refueling Seifu got away and applied for asylum and remained in Canada.

Finally in 1980 he came to Los Angeles, CA where he joined his nephew and called it home until his passing. His most cherished accomplishment is the yearly 10,000 meter race that is held in Washington DC he started and named it after the great marathoner Abebe Bikila. Tibo was a hard worker, ready to help anyone, a great listener. He was a gentle giant with a golden heart and loved by everybody.

Seifu was one of the first board members of Virgin Mary Ethiopian Orthodox Church here in LA and served for over five years. He was married and blessed with two children. Much to the loss of many, and after months of battling a challenging illness Seifu Tibo passed away on Tuesday June 16, 2020 at the age of 67. He is survived by his kids, his mom, two sisters and a grad son.

May he Rest In Eternal Peace!